ጸሐፊ፡ abuki ከ turkey

የ outlier ቤተሰቦች ይህን ፎቶ የማያውቅ ጥቂቶች ናቹ መቼስ።

ከኤርትራ ብሄረሰቦች መካከል "ትግረ" ከሚባለው ብሄር ነው የተወለደው ብዙ የዓለም ክፍሎች ከፍተኛ ዝና ለመጎናጸፍ የቻለው ኤርትራዊም ከዚህ ህዝብ ነው የተወለደው የኖረው ሳቂታው የበኒ ዐምር ወጣት ነው፡፡
የበኒ ዐምሩ ወጣት ለብዙ ዓመታት አነጋጋሪ ሆኖ ዘልቋል፡፡ ወጣቱ የበርካቶች መነጋገሪያ ለመሆን የበቃው ፖስተሩ የሚታወቀውን ያህል ማንነቱ በደንብ ስለማይታወቅ ነው፡፡ ፎቶግራፍ ያነሳው ለአሜሪካው ናሽናል ጂኦግራፊክ ሶሳይቲ ይሠራ የነበረ ጀምስ ብሌር የሚባል የፎቶ ጋዜጠኛ ነው፡፡ ብሌር ፎግራፉን ያነሳው እ.ኤ.አ. በ1965 በያኔዋ ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ (በአሁኗ ኤርትራ ምዕራባዊ ክፍል) በምትገኘው የተሰነይ ከተማ አቅራቢያ ነው፡፡ እ.ኤ.አ. በ1989 አርፏል፡፡ ይህም የዛሬ 29 ዓመት ገደማ መሆኑ ነው፡፡ ወጣቱ ፎቶውን ሲነሳ በግምት አስራ ሰባት ዓመት ሆኖት እንደነበረ ይገመታል፡፡

ተጻፈ:- jul/29/2025

image